የሰላም ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) “ለሁላችንም የምትመች ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሰላም ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንሱ የተዘጋጀው በአማራ እና ኦሮሞ ባለሃብቶች ኮሚቴ የተዘጋጀ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሀይማኖት መሪዎች የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች እና ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛል።
በኮንፈረንሱ የሰላምን አስፈላጊነት የሚያጎሉ መልዕክቶች ይተላለፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኮንፈረንሱ ባለፉት ሳምንታት በአማራና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥታት የንግድ ማኅበረሰብ፣ የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን አንቂዎች፣ ወጣቶች፣ የሃይማኖትና የማህበረሰብ አመራሮች መካከል ሲካሄዱ የቆዩት ጉባኤያት ማጠናከሪያ ነው።
ጉባኤያቱ ልዩነቶችን አስታርቆና አቻችሎ የሁለቱን ክልል ሕዝቦች ለማቀራረብ ታስበው የተዘጋጁ ናቸው።
በሀብታሙ ተክለስላሴ