Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር ሽልማትን አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በፋይናንሺያል አፍሪክ መጽሄት የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር ሽልማት ተበረከተላቸው።

ፋይናንሺያል አፍሪክ በፓሪስ የሚታተም መጽሔት ሲሆን፥ ትናንት በአቢጃን ከተማ በተካሄደ ስነ ስርዓት የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴን የዓመቱ የፋይናንስ ሚኒስትር በማለት ሽልማት አበርክቶላቸዋል።

በኮትዲቯር የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙሉጌታ ዘውዴ ሚኒስትሩን ወክለው ሽልማቱን ተቀብለዋል።

መጽሔቱ በየዓመቱ ከ100 ዕውቅ የገንዘብ፣ የፋይናንስና ኢኮኖሚ መሪዎች ምርጫ እንደሚያካሂድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በኢኮኖሚክስ መስክም ካርሎስ ሎፔስን የዓመቱ ኢኮኖሚስት ብሎ ስይሟቸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.