Fana: At a Speed of Life!

በዓለም የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ27 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ27 ሚሊየን ማለፉ ተነግሯል።

እንደ ጆንሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እስካሁን በአለም አቀፍ ደረጃ ከ27 ሚሊዮን የሚልቁ ሰወች በወረርሽኙ መያዛቸውን ያሳያል፡፡

እስካሁን በቫይረሱ ከ880 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወትም ማለፉም የተነገረ ሲሆን፥ ከ18 ሚሊየን በላይ ሰዎች ማገገማቸውም ተሰምቷል።

በርካታ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን በመያዝ አሁንም አሜሪካ በቀዳሚነት የተቀመጠች ሲሆን፥ ህንድ ብራዚልን በመብለጥ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፤ ብራዚል ደግሞ 3ኛ ደረጃ ላይ ነው የምትገኘው።

ምንጭ፦ ሲ.ጂ.ቲ.ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.