ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሱዳን ልዑላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አስመራ ገቡ

By Tibebu Kebede

September 07, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ልዑላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ገብተዋል።

ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አስመራ የገቡት ሊቀመንበሩ በኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል እንደተደረገላቸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።