Fana: At a Speed of Life!

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሯ ከቻይና የኮንስትራክሽን ተቋማት ፕሬዚዳንቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ከቻይና መንግስት የኮንስትራክሽን ተቋማት ፕሬዚዳንቶች እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

በውይይቱ በመጭዎቹ 10 ዓመታት ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ልትደርስበት ያሰበችውን ዕቅድ በተመለከተ የተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት ተደርጓል።

የቻይና የኮንስትራክሽን ተቋማት ኢትዮጵያ በዘርፉ እያከናወነች ባለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚኖራቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተመላክቷል።

በቤቶች ልማትና በመሰረተ ልማት ዘርፎች መንግስት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት መሰረት በማድረግም ተቋማቱ የሚኖራቸው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ በትብብር መስራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ምክክር ተደርጓል።

የልዑካን ቡድኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ኢትዮጵያ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ መሆኗን ጠቅሰው በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል።

በተጨማሪም ልዑካኑ ዛሬ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋን ሳተላይት በማምጠቋ የእንኳን ደስ አላችሁ መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.