የሀገር ውስጥ ዜና

ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በማያጋልጥ መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስጀመር ጥናት ተደርጓል- ትምህርት ሚኒስቴር

By Tibebu Kebede

September 08, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሊያጋልጥ በማይችልና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የመማር ማስተማር ሂደቱን በአዲሱ ዓመት ለማስጀመር ጥናት መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስተር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ፥ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን አመልክተዋል።