ስፓርት

አርቴታ አርሰናልን በአሰልጣኝነት ተረከበ

By Tibebu Kebede

December 20, 2019

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዙ እግር ኳስ ክለብ አርሰናል ሚካኤል አርቴታን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን አስታወቀ።

ክለቡ የቀድሞ አማካዩን በዋና አሰልጣኝነት ለመቅጠር ለማንቼስተር ሲቲ በሚሰጠው የካሳ ክፍያ ዙሪያ ስምምነት ላይ መድረሱም ነው የተነገረው።

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አሰልጣኝ ኡናይ ኢምሬን ካሰናበተ በኋላ የክለቡን የቀድሞ ተጫዋች ፍሬዲ ሊዩንበርግን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ቀጥሯል።

ክለቡ የገባበት የውጤት ቀውስ ለአሰልጣኝ ሹም ሽር ምክንያት ሆኖታል።

አርሰናል በፕሪሚየር ሊጉ በ22 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የቀድሞው ስፔናዊው አማካይ በማንቼስተር ሲቲ የአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ረዳት በመሆን እየሰራ መቆየቱ ይታወሳል።