የሰላም ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) “ለሁላችንም የምትመች ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሰላም ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ ተካሄደ።
ሀገር አቀፍ የሰላም ኮንፈረንሱ የተዘጋጀው በአማራ እና ኦሮሞ ባለሃብቶች ኮሚቴ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኮንፈረንሱ ላይ ተገኝተዋል።
በኮንፈረንሱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሀይማኖት መሪዎች የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች እና ወጣቶች ተሳትፈዋል።
በኮንፈረንሱ የሰላምን አስፈላጊነት የሚያጎሉ መልዕክቶች የተላለፉ ሲሆን፥ ባለፉት ሳምንታት በአማራና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥታት የንግድ ማኅበረሰብ፣ የማህበረሰብ አንቂዎች፣ ወጣቶች፣ የሃይማኖትና የማህበረሰብ አመራሮች መካከል ሲካሄዱ የቆዩት ጉባኤያት ማጠናከሪያ ነው።
ጉባኤያቱ ልዩነቶችን አስታርቆና አቻችሎ የሁለቱን ክልል ሕዝቦች ለማቀራረብ ታስበው የተዘጋጁ ናቸው።
በሀብታሙ ተክለስላሴ