Fana: At a Speed of Life!

ቦሪስ ጆንሰን ሃገራቸውን ከአውሮፓ ህብረት በጥር ወር መጨረሻ ለማስወጣት ያቀረቡት እቅድ በፓርላማ አባላቱ ጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 10 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሪታንያ ፓርላማ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሃገራቸውን በመጭው ወር መጨረሻ ከህብረቱ ለማስወጣት ያቀረቡትን እቅድ ደገፉ።

አባላቱ በረቂቁ ላይ በሰጡት ድምጽ እቅዱን 358 ለ234 በሆነ ድምጽ አዕድቀውታል።

በአባላቱ ድጋፍ ያገኘው እቅድ በፓርላማው ውይይትና ክርክር ይደረግበታል ተብሏል።

አባላቱ ከአዲስ አመት መልስ ባለው የመጀመሪያው ሳምንት መጨረሻ ቀናት ላይ በረቂቁ ላይ ክርክር ለማድረግ ተስማምተዋል።

በፓርላማው ወግ አጥባቂው የቦሪስ ጆንሰን ፓርቲ አብላጫ መቀመጫ እንደመያዙ በቀላሉ ይሁታን እንደሚያገኝ ይጠበቃል።

ድምጽ የተሰጠበት የጠቅላይ ሚኒስትሩ እቅድ ብሪታንያ ከህብረቱ ጋር የምትፈጽመውን ፍቺ ለተጨማሪ ጊዜ ማራዘምን ሊከለክል ይችላል ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን ብሪታንያን ከአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹ ጥር 31 ለማስወጣት እቅድ አላቸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.