የሀገር ውስጥ ዜና

በ2013 ዓ.ም የብልጽግና መሰረትን የመጣል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል – የብልጽግና ፓርቲ

By Feven Bishaw

September 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ የብልጽግና መሰረትን የመጣል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የብልጽግና ፓርቲ አስታወቀ፡፡

የፓርቲው የጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ 1 ቀን ብቻ በቀረው 2012 ዓ.ም የሀገሪቱን ህልውና የተፈታተኑ ችግሮችን መሻገር ተችሏል። ለውጡን ለማደናቀፍ እና በሀገር ህልውና ጭምር የመጣ የጥፋት እንቅስቃሴ ሀገሪቱን ዋጋ አስከፍሎ አልፏል።