147 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ በሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በተለያዩ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 147 ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያዊያኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳዮች ዳ/ጄኔራል ወይዘሮ አልማዝ ገበያውን ጨምሮ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተወከሉ ባለሙያዎች ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።