የሀገር ውስጥ ዜና

147 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ

By Meseret Demissu

September 10, 2020

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ በሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በተለያዩ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 147 ኢትዮጵያዊያን  ዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን 2012 ዓም ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

ኢትዮጵያዊያኑ  ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጉዳዮች ዳ/ጄኔራል ወይዘሮ አልማዝ ገበያውን ጨምሮ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተወከሉ ባለሙያዎች ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።