ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በቀድሞ ከንቲባ ኢ/ር ዘውዴ ተክሌ መኖሪያ ቤት በመገኘት የበዓል ስጦታ አበርክተዋል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 1፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በቀድሞ ከንቲባ ኢ/ር ዘውዴ ተክሌ መኖሪያ ቤት በመገኘት እንኳን አደረሰዎት ብለዋል።
ኢንጂነር ዘውዴ ተክሌ ከ1973 እስከ 1981 ዓ.ም ለሰባት ዓመታት አዲስ አበባን እና ነዋሪዋን በከንቲባነት አገልግለዋል።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች ኢንጂነር ዘውዴን በመኖሪያ ቤታቸው በመገኘች የእንኳን አደረሰዎት መልዕክት እና የበዓል ስጦታ አበርክተዋል።
ኢንጂነር ዘውዴ በስልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜያት ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪን በቅንነት ስላገለገሉ ወይዘሮ አዳነች ምስጋና አቅርበውላቸዋል።
ምክትል ከንቲባ አዳነች ከእርሳቸው ትምህርት እና ምክር ለመውሰድ በድጋሚ እንደሚጎበኙአችውም ተናግረዋል።
ኢንጂነር ዘውዴ በበኩላቸው ወይዘሮ አዳነች በታሪክ የመጀመሪያ ሴት ከንቲባ በመሆናቸው የተሰማቸውን ደስታ የገለጹ ሲሆን፥ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ተመኝተዋል።
ኢንጂነር ዘውዴ እና ቤተሰቦቻቸው ለወይዘሮ አዳነች የበዓል ስጦታ ማበርከታቸውን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሰክረተሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በጉብኝቱ ላይ ወይዘሮ አዳነችን ጨምሮ፣ አቶ ጃንጥራር አባይ፣ አቶ መለስ አለም እንዲሁም ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።