የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 የብር ኖቶች የሚተኩ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶችና አዲሱን የ200 ብር ኖት ይፋ አደረገች

By Tibebu Kebede

September 14, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር ኖቶች ዓይነቶችን ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የብር ኖት መጠቀም እንደምትጀምር ይፋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

ነባሮቹን የብር ኖቶች ከሚተኩት በተጨማሪ በዛሬው ዕለት የ200 ብር ኖት ይፋ እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በፌስቡክ ገፃቸው ባወጡት መረጃ የገለፁት።