ዓለምአቀፋዊ ዜና

ዮሲሂዴ ተሰናባቹን የጃፓን ገዢ ፓርቲ መሪ ሺንዞ አቤን በመተካት የፓርቲው መሪ በመሆን ተመረጡ

By Abrham Fekede

September 14, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዮሲሂዴ ሱገ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትርና የገዢው ፓርቲ መሪ ሺንዞ አቤን በመተካት የጃፓን ሊበራል ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪ በመሆን ተመረጡ፡፡

ዮሲሂዴ ሱገ የፓርቲው መሪ ሆነው በመመረጣቸው ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የሚያደርጉትን ጎዞ ያቀልላቸዋል ተብሏል፡፡

የ71 ዓመቱ ዮሲሂዴ ዛሬ ይፋ በሆነው ምርጫ በቀላሉ ማሸነፋቸው ተነግሯል፡፡

በዚህም ከ534 ድምጽ ውስጥ 337 ድምጽ ማግኘታቸውን አልጀዚራ ዘገቧል።

ዮሲሂዴ ሱገ ተፎካካሪዎች የመከለከያ ሚኒስትሩ እና የቀድሞ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፉምዮ ኪሺዳ እንደነበሩ ተሰምቷል፡፡

ረቡዕ በሚካሄደው ፓርላመንታዊ ምርጫ ከወዲሁ እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል፡፡

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በህመም ምክንያት በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸው የሚታወስ ነው፡፡