Fana: At a Speed of Life!

ታላቁ ህዳሴ ግድብ በደለል እንዳይሞላ አስቀድሞ ለመከላከል የተጀመሩ የተፋሰስ ልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 11፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ታላቁ ህዳሴ ግድብ በደለል እንዳይሞላ አስቀድሞ ለመከላከል የተጀመሩ የተፋሰስ ልማት ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ላይ የሚመክር ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ በመቐለ ከተማ  እየተካሄደ ነው።

ለአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ህይወት ዘላቂነትና ሀገሪቱ ህዳሴ ጉዞ መረጋገጥ በከፍተኛ ወጪ የሚገነቡ የውሃ ግድቦች በደለል እንዳይሞሉ መከላከል ይገባል ሲሉ የታለቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሮማን ገብረስላሴ  አስገነዘቡ።።

ባለፉት ዓመታት በሁሉም አካባቢ ለተፋሰስ ልማት ስራዎች በተሰጠው ትኩረት 81 ቢሊዮን ብር ግምት ያላቸው ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ  ህዝቦች አንድነትና መተባበርን በተግባር ያረጋገጠው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ስራ 69 ነጥብ 7 በመቶ ደረጃ ላይ  መድረሱም ተገልጿል፡፡

ለሶስተኛ ጊዜ እየተካሄደ ባለው ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ  በኢትዮጵያ በውሃ ግድቦችና በተፋሰስ ልማት ስራዎች ላይ ያተኮሩ  አምስት ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው  ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.