የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከገበታ ለሀገር አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

September 16, 2020

አዲስ አበባ ፣መስከረም 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለኮይሻ፣ ወንጪ እና ጎርጎራ የልማት ፕሮጀክቶች የገቢ ማሰባሰቢያ እንቅስቃሴን በተመለከተ ከገበታ ለሀገር አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ተወያዩ።

የመንግሥት ሠራተኞች የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለዚሁ ተግባር እየለገሱ መሆኑ በውይይቱ ወቅት መነሳቱን ከጠቅይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።