የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ ምሽት 2 ሰዓት ከባድ ተሽከርካሪ ማስገባት እና ማንቀሳቀስ እንደሚያስቀጣ ተገለፀ

By Tibebu Kebede

September 16, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ ምሽት 2ሰዓት ከባድ ተሽከርካሪ ማስገባት እና ማንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን የከተማዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ።

መመሪያውን ተላልፈው የተገኙ አሽከርካሪዎች ከ500 እስከ 6 ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ ኤጀንሲው ገልጿል ።