ዓለምአቀፋዊ ዜና

የናይጄሪያዋ ግዛት ህፃናትን የሚደፍሩ ግለሰቦች እንዲኮላሹ የሚያደርግ ህግ አጸደቀች

By Abrham Fekede

September 17, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሰሜናዊ ናይጄሪያ የምትገኘው ካዱና ግዛት ህጻናትን የሚደፍሩ ግለሰቦች በህክምና እንዲኮላሹ የሚያደርግ ህግ አጸደቀች፡፡

የካዱና ገዢ ናስር አህመድ ኤል ሩፋይ አዲሱ የወጣው ህግ ላይ ትናንት ማምሻውን ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

አዲሱ ህግ ከ14 ዓመት በታች የሚገኙ ህጻናት ደፋሪዎችን በህክምና እንዲኮላሹ ከማድረግ በተጨማሪ የእድሜ ልክ እስራት እንደሚጠብቃቸው ነው የተገለጸው፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመላው ናይጄሪያ አስገድዶ መድፈርን የሚቃወሙ ዘመቻዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የሀገሪቱ መንግስት ጠርጥሬያቸዋለው ያላቸውን ሰዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተነግሯል፡፡

አዲሱን ህግ ያጸደቀችው ካዱና ግዛት ይህንን ውሳኔ ስታሳልፍ በናይጄሪያ ከሚገኙ ግዛቶች መካከል ብቸኛዋ መሆኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡