የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 29 ሚሊየን ብር የሚገመት በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ ተደረገ

By Tibebu Kebede

September 18, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 29 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ከተማ አስተዳደር በጀት፣ የብልጽግና ወጣቶች ሊግ፣ በጎፍቃደኞች እና አሚባራ ኃ.የ.ግ.ማ የተሰበሰበ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።