የሀገር ውስጥ ዜና

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሁለት ወራት 42 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

By Feven Bishaw

September 18, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በ2013 በጀት አመት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት 42 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስቴሩ የስራ ኃላፊዎች የ2013 በጀት አመት የገቢ አሰባሰብ እቅድ እና በበጀት ዓመቱ የሁለት ወራት አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡