በጉደር የሚገኘውን የአምቦ ሰብ ስቴሽን ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ)የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በጉደር የሚገኘውን የአምቦ ሰብ ስቴሽንን መርቀዋል።
ለአምቦና አካበቢዋ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ የተገነባው ሰብ ስቴሽን 50 ሜጋ ዋት ሀይል መሸከም የሚችልና 110 ሚሊየን በላይ ወጭ የተደረገበት መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ÷ የኤሌክትሪክ አገልግሎቱን በምዕራብ ሸዋ ዞን እና አምቦ አካባቢ ተደራሽ ለማድረግ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።
በምርቃት ስነስርአቱ ንግግር ያደረጉት አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷ በክልሉ አጠቃላይ 9 ሰብ ሰቴሽኖች በመገንባት እና ለመገንባት በዝግጅት ላይ እንዳሉ ገልፀዋል።
ሰብ ስቴሽኖቹ ለህዝቡ ብርሃን ከመስጠት ባለፈ በዋናነት ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ታቅደው ተግባራዊ የተደረጉ ናቸውም ነው ያሉት።
ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም ከ9ኙ መካከል አንዱ የሆነው የአምቦ ሰብ ስቴሽን ለአምቦና አካባቢው ኢንደስትሪ መስፋፋት ከፍተኛ ጥቅም ይኖረዋል ብለዋል።
ሰብ ስቴሽኑ በፍጥነት የተጠናቀቀ መሆኑን የገለፁት አቶ ሽመልስ ÷ የለውጡ መንግስት እየሰራ የለው መጀመር ብቻ ሳይሆን መጨረስን ባህል ለማድረግ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ለምናስበው ብልጽግና መሰረተ ልማቶቹ እጅጉን ያስፈልጉናል ያሉት አቶ ሽመልስ መስራትና መለወጥ ካልተቻለ ግን ዋጋ አይኖራቸውም ስለሆነም መስራት ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።
በሀብታሙ ተ/ስላሴ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።