የሀገር ውስጥ ዜና

ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

By Meseret Demissu

September 20, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10 ፣ 2013(ኤፍ.ቢ.ሲ)የአፋር ክልል ፕሬዚደንት በመሆን ያገለገሉት ሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ይህንንም ተከትሎ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በሱልጣን ሀንፈሬ አሊሚራህ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት የሀዘን መግለጫ÷ ”የአፋር ክልል ፕሬዚደንት በመሆን፣ ቀጥሎም ለኩዌት አምባሳደር በመሆን፣ እስከ ግዞታቸው ድረስ  ሀገራቸውን ያገለገሉት ሱልጣን ሐንፍሬ አሊ ሚራ ማለፋቸውን በመስማቴ እጅግ አዝኛለሁ። ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጆቻቸው መጽናናትን እመኛለሁ”ብለዋል።