Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል በወራቤ ከተማ ከህዝቡ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ የተለያዩ የፌደራል እና የስልጤ ዞን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ከዞኑ ነዋሪዎች ጋር በወራቤ ከተማ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በዞኑ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር እና የመሰረ ልማት ችግሮችን መፍታት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እንዲሁም ከመሰረተ ልማት ዝርጋት ጋር በተያያዘ በውሃ፣ መንገድ እና መብራት አገልግሎት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን አንስተዋል።

የዞኑ አስተዳደሪ አቶ አሊ ከድር በምላሻቸው፥ ከተሳታፊዎች የተነሱ የመልካም አስተዳዳር እና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ችግሮችን ለመቅረፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ መሰረትም ለችግሮች መፈጠር ምክንያት የሆኑ አመራሮችን በማንሳት በምትኩ እንደ አዲስ አመራሮችን የማዋቀር ስራ መከናወኑን ነው የገለጹት።

ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው በዞኑ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ችግሮችን ለመፍታት በጥናት የተደገፈ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።

ለዚህም የፊታችን ሀሙስ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ወደ ዞኑ በማቅናት ምልክታ የሚያደርጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

መንግስት አሁን ላይ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ከመጀመር ይልቅ የተጀመሩትን ለመጨረስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነም አስረድተዋል።

መንግስ ከሚሰጠው ምላሽ በተጨማሪም የዞኑ ነዋሪዎች እና የብሄሩ ተወላጆች እንደ ከዚህ በፊቱ በልማት ስራዎች ላይ የሚያድርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ነዋሪዎች በዞኑ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር እና የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን በሰለጠነ መንገድ ለውይይት ማቅረባቸውን አድንቀዋል።

በጥበበስላሴ ጀምበሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.