የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ መስጠት ጀመረ

By Tibebu Kebede

September 22, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ መስጠት መጀመሩ ተገለፀ።

ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ድግሪ ደረጃ መስጠት የጀመረበት የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትም በቤጂንግ መካሄዱን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሰዲ መረጃ ያመለክታል።