የሀገር ውስጥ ዜና

በመተከል ዞን የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በሁሉም ወረዳዎች የአመራር ግምገማ ከነገ ጀምሮ ይካሄዳል

By Meseret Demissu

September 22, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመተከል ዞን የሚስተዋሉ የጸጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከነገ ጀምሮ በሁሉም ወረዳዎች የአመራር ግምገማ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በቅርቡ የጸጥታ ችግር የተፈጠረባቸውን ወምበራና ቡለን ወረዳዎች ጨምሮ በመተከል ዞን ሁሉም ወረዳዎች ዘላቂ ሠላምን ለመገንባትና የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ የአመራር ግምገማ እንደሚካሄድ ነው የክልሉ መንግስት ያስታወቀው።