251 ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 251 ኢትዮጵያዊያን ዜጎቻችን ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓም ከሳኡዲ አረቢያ ጄዳ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያዊያኑ በሳኡዲ አረቢያ በሚገኙ እስር ቤቶች እና በተለያየ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያውያኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርሱ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ከሚመለከታው መስሪያ ቤቶቸ የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ባሳለፍነው ሳምንትም በሳኡዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በተለያዩ ችግር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 274 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ መመለሳቸው ይታወሳል።