Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ለመስቀል ደመራ በዓል ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  መሰከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የሚከበረው የደመራ በዓል ተጀምሮ አስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግየሚደረጉ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት፦

 ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ

 ከመገናኛ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ

 ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት

 ከቸርችል ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አገር አስተዳደር መብራት ወይም ኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት አካባቢ

 ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ

 ከተክለ ሀይማኖት፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፣ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ

 ከጌጃ ሰፈር፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ

 ከሳሪስ በጎተራ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ

 ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ

 ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ፣ ሜክሲኮ ፣ ለገሀር መብራት የሚወስደው መንገድ ለገሃር መብራት አካባቢ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም ደመራው የሚደመርበት መስቀል አደባባይ እና ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ስታዲየም እንዲሁም ከሃራምቤ ሆቴል ወደ ሴንጅ ዮሰፍ የሚያቋርጠው መስቀለኛ መንገድ ለበዓሉ በሚደረገው ዝግጅት ምክንያት ከጠዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ የሚደረግ መሆኑን አስታውቋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ከፖሊስ የተሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.