ለአቶ ልደቱ አያሌው የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈቀደው የ100 ሺህ ብር የዋስትና ፈቃድ ታገደ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለአቶ ልደቱ አያሌው ከትናንት በስቲያ የምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፈቀደው የ100 ሺህ ብር የዋስትና ፈቃድ ታገደ፡፡
ዋስትናውን ያገደው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ሸዋ ተዘዋዋሪ ምድብ ችሎት ነው፡፡
እግዱም በአዳማ ፍትህ ቢሮ አቃቤ ህግ ዋስትናው ላይ ይግባኝ ተብሎ ሲሆን÷ ፍርድ ቤቱ ይግባኝ ያስቀርባል ሲል ዋስትናውን በማገድ መስከረም 19 በቀጠሯቸው እንዲቀርቡ አዟል፡፡
አቶ ልደቱ አያሌው ያልተፈቀደ የጦር መሳሪያ በመያዝ ወንጀል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡
በታሪክ አዱኛ