ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ጋር በስልክ ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ ለፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ባደረጉት የስልክ ጥሪ በተለያዩ የሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ መወያየታቸውን የፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።
ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ በግድቡ ዙሪያ ላደረጉት ተጨማሪ ማብራሪያ አመስግነዋል።
ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ የአፍሪካ ህብረት ለሚመራው ውይይት ያላትን ቁርጠኝነት ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ አረጋግጠዋል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።