Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው አይ ኤስ ቡድን በኢራቅ ዳግም እየተጠናከረ መምጣቱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሸባሪው ኡስላሚስ ስቴት (አይ.ኤስ) ቡድን በኢራቅ  እንደገና እየጠናከረ መሆኑ ተሰምቷል።

የእስላማዊ መንግስት (አይ.ሲ.ስ) ቡድን በኢራቅ የመጨረሻ ግዛቱን ካጣ ከ2 ዓመት በኋላ እየተደራጀ መሆኑን የሚያመላክቱ መረጃዎች እየታዩ መሆናቸው  ነው የተነገረው።

በአካባቢው የአይ.ኤስ ጥቃቶች እየጨመሩ መምጣታቸውን  ተነግሯል።

የአሸባሪው አይ ኤስ ታጣቂ ቡድኖች በአሁን ሰዓት ከአልቃይዳ የበለጠ አደገኛ መሆናቸውን ላሁር ታላባኒ የኩርድ ከፍተኛ ባለስልጣን ገልጸዋል።

በቴክኒክ፣ በታክቲክ እና በገንዘብ የተሻለ አቅም ስላላቸውም ተሸከርካሪዎችን፣ የጦር መሳሪያዎችን፣ የምግብ አቅርቦቶችን በቀላሉ በሟሟላት ራሳቸውን ያደራጁ በመሆኑ እነሱን በቀላሉ ማስወጣት ከባድ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ይህ እንደ አዲስ ብቅ ያለው ታጣቂ ቡድኑ የጥቃት ኢላማ እንዳይሆን የትኛውንም አካበባቢ የመቆጣጠር ፍላጎት የሌለውና በኢራቅ ሐሚሪን ተራሮች ውስጥ መሽጎ እንደሚገኝ ተነግሯል።

እነዚህ ረጃጅም ተራሮች  ለአሸባሪው አይ ኤስ ቡድን እንደማዕከል ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

ተራሮቹ ለመደበቅ የሚያስችሉ በርካታ ዋሻዎች ስላሏቸው የኢራቅ ጦር ለመቆጣጠር በጣም ከባድ መሆኑን ነው የተነገረው።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.