Fana: At a Speed of Life!

ለሆቴል ሩዋንዳ ፊልም መሰራት ምክንያት የነበሩት ፖል ታጣቂ ኃይል መመስረታቸውን አመኑ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሆቴል ሩዋንዳ ፊልም መሰራት ምክንያት የነበሩት ፖል ሩሴሳባጊና ታጣቂ ኃይል መመስረታቸውን ኪጋሊ ለሚገኘው ፍርድ ቤት ማመናቸው ተሰምቷል፡፡

ሩሴሳባጊና ታጣቂ ኃይል መመስረታቸውን ቢያምኑም ታጣቂዎች ከፈጸሙት ጥቃት ጋር በተያያዘ ምንም ሚና አልነበረኝም ብለዋል፡፡

በአውሮፓውያኑ 1994 በሩዋንዳ ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች ያለቁበት የዘር ፍጅት መከሰቱ የሚታወስ ነው፡፡

በዚህ ወቅትም የሁቱ ተወላጅ የነበሩት ፖል ሩሴሳባጊናም ሆቴል ሩዋንዳ በሚሰኘው ሆቴላቸው ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ቱትሲዎችን ከጥቃት መታደጋቸው ይነገራል፡፡

በዚህም ምክንያት 2004 ላይ ጀግነነታቸውን የሚያሳይ ሆቴል ሩዋንዳ የተሰኘ ፊልም ለዕይታ በቅቷል፡፡

ሩሴሳባጊና በፖለቲካው ዓለም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መቀመጫውን ከሀገር ውጪ ያደረገ ፓርቲ መስርተው እንደነበር ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም የሩዋንዳ ነጻነት ግንባር በሚል ለሚዋጋ ታጣቂ ኃይል ድጋፍ መቸራቸውም ተሰምቷል፡፡

ፖል ሩሴሳባጊና በነሃሴ ወርም ዓለም አቀፍ የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸው በሽብር ተከሰው በቁጥጥር ስር ለመዋል በቅተዋል፡፡

ምንጭ፡-ኤኤፍፒ

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.