Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቻይና ከአንድ ሰው ጭንቅላት 5 ሴንቲ ሜትር ርዝመትያላቸው መርፌዎች ተገኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በቻይና በአንዲት ወጣት ጭንቅላት ውስጥ ርዝመታቸው በግምት 5 ሴንቲ ሜትር የሆነ ሁለት መርፌዎች መገኘታቸው ተሰምቷል፡፡

ወጣቷ ይህን ያወቀችው የደረሰባትን የመኪና አደጋ ተከትሎ የሲቲ ስካን ምርመራ ስታደርግ መሆኑ ታውቋል፡፡

የተገኘው መርፌ በአደጋው ወቅት ወደ ጭንቅላቷ የገባ ወይም ከአደጋው ጋር ምንም የሚገናኝ አለመሆኑም ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ወጣቷ በሕይወቷ በማንኛውም ወቅት ምንም ዓይነት ከባድ የጭንቅላት አደጋ አጋጥሟት አያውቅም ነው የተባለው፡፡

ዶክተሮቹ መርፌው በአጋጣሚ ወይም ሆን ተብሎ ወደ ጭንቅላቷ የገባ ነው ብለው እንደሚያምኑ ነው የተናገሩት፡፡

ወጣቷ የራስ ምታት አጋጥሟት እንደማያውቅ የተናገረች ሲሆን መርፌዎቹ ምንም ዓይነት ችግር እንደማያስከትሉ መረጋገጡንም ተናግራለች፡፡

ምንጭ፡- ኦዲቲ ሴንትራል

Exit mobile version