የትራንስፖርት ሚኒስቴር እያስመዘገበ ላለው የተሻለ አፈጻጸም እውቅና ተሰጠው
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (አፍ.ቢ.ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስቴር እያስመዘገበ ላለው የተሻለ አፈጻጸምና ላሳየው አጋርነት ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ ከተባለ ተቋም እውቅና ተሰጠው።
መቀመጫውን ናይሮቢ ያደረገው ትሬድ ማርክ ኢስት አፍሪካ፥ የምስራቅ አፍሪካ ሃገራትን ትስስር ለማጠናከር ትኩረቱን በትራንስፖርትና ንግድ ዘርፍ ላይ አድርጎ የሚሰራ ነው።
ተቋሙ በየአመቱ በሚያዘጋጀው አመታዊ ጉባዔ ላይ በምስራቅ አፍሪካ በአጋርነት ከሚሰሩ አቻ ተቋማት ውስጥ ለኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር፥ በ2019 ባስመዘገበው የተሻለ አፈጻጸምና ላሳየው አጋርነት እውቅና መስጠቱን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።