ቴክ

የቻይና ስነ ፈለክ ተመራማሪዎች የመጀመሪዋን ከፀሀይ ስርዓት ውጪ የሆች ኤክሶፕላኔት አገኙ

By Tibebu Kebede

December 23, 2019

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ስነ ፈለክ ተመራማሪዎች የመጀመሪዋን ከፀሀይ ስርዓት ውጪ የሆች ኤክሶፕላኔት ማግኘታቸው ተገለፀ።

በቻይና የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች የተገኘችው ይህች ፕላኔት  “ወንግሹ” እና “ዢሂ” የሚል ስያሜ ተሰቷታል።

ይህም ማለት የጨረቃ አምላክ ወይም የጸሃይ አምላክ የሚል ትርጉም አለው።

ሁለቱ ስሞች የሚያሳዩት የኮኮብ እና ፕላኔትን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን ዩንቨርስን የማሳስ ሂደት የሚወክል ወይም ምሳሌ የሚሆን ነው ተብሏል።

የፕላኔትዋ መጠን ከፀሐይ ሁለት እጥፍ የሚበልጥ ሲሆን፥ ከጁፒተርም በ2 ነጥብ 7 እጥፍ ትበልጣለች፤ በዚህም ከጸሃይ ስርዓት ውስጥ ትልቋ ነው የተባለችው በብሔራዊ የሥነ ፈለክ ምርምር ተቋም።

የቻይና የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች በአውሮፓውያኑ በ2008 ከቻይና 10 ምርጥ የሥነ ፈለክ እድገቶች መካከል አንዱ ሆነው የተመረጡት ትልቁን ኤክስፕላኔት HD173416b’ን አገኝታለች።

ምንጭ፡-ሲጂቲኤን

በፌቨን ቢሻው