Fana: At a Speed of Life!

የአልጄሪያ ጦር አዛዥ ጄነራል አህመድ ጋይድ አረፉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአልጄሪያ ጦር አዛዥ ጄነራል አህመድ ጋይድ ሳላህ ማረፋቸው ተነገረ።

ጋይድ ሳላህ ዛሬ ጠዋት በአልጀርስ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ በልብ ድካም ህይወታቸው ማለፍን የሀገሪቱ የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የ79 ዓመቱ ጄነራል ጋይድ ሳህሌ በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ ወር ላይ ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቦትፍሊካን በመቃወም በተካሄደው በድብቅ የዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ድጋፍ በማድረጋቸው በአልጄሪያ እንደ አንድ ጠንካራ ሰው እንደሚታዩ ተነግሯል።

በጎዳናዎች ላይ ጠንካራ ተቃውሞ በየታየበት በታህሳስ 12ቱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ የማይተካ ቁልፍ ሚና ተጫውቷል ተብሏል።

ጋይድ ሳህሌ ባለፈው ሳምንት በተከናወነው የአዲሱ ፕሬዝዳንት አብደልመጂድ ታቡን በዓለ ሲመት ላይ ተገኝተው እንደነበረም ተገልጿል።

አዲሱ ፕሬዝዳንት አብድልመጂድ ታቦአኒ የጦር አዛዡን ህልፈት ተከትሎ በሀገሪቱ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ የሀዘን ቀን ማወጃቸው ነው የተነገረው።

የምድር ጦር ሀላፊው ጄኔራል ሰኢድ ቼንግሪ በጊዜያዊነት የአልጄሪያ ጦር ጠቅላይ ኢታማዦር ስፍራን ተክተው እንደነሚሰሩም ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.