ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሴራሊዮን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ

By Meseret Demissu

September 30, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሴራሊዮን የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኧርነስት ባይ ኮሮማ  ከሀገር እንዳይወጡ ታገዱ።

የሃገሪቱ መንግስት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ጨምሮ በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ባገለገሉ ከ100 በላይ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ላይ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የጉዞ እገዳ መጣሉን አስታውቋል፡፡

መንግስት ግለሰቦቹ መዝብረውታል ያለውን ገንዘብ እንዲመልሱና ቤቶቻቸውን እንዲያስረክቡም ትዕዛዝ  ሰጥተቷል፡፡

ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን ተጨማሪ ምርመራ ይደረግባቸዋል ነው የተባለው፡፡

ሆኖም የቀድሞው ፕሬዚዳንት የመላው ሕዝቦች ኮንግረስ (ኤ.ፒ.ሲ) ፓርቲ ውንጀላውን አስተባብሏል።

ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደውም የፓርቲው ጠበቃ ተናግረዋል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።