የሀገር ውስጥ ዜና

የእናቶች፣ ወጣቶችና የህጻናት ጤና አቅርቦት እንዳይጓደል በአንድነት መስራት ይገባል – ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ

By Abrham Fekede

October 01, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የእናቶች፣ የወጣቶችና የህጻናት ጤና አቅርቦት እንዳይጓደል ሁሉም በአንድነት መስራት እንዳለበት ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቷ የእናቶች፣ የጨቅላ ህጻናት እና የልጆች ጤና አጋርነት በተባለ ድርጅት በተዘጋጀ ዉይይት ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ለእናቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ጤና እንዳይጓደል ሁሉም መስራት ይገባዋል ብለዋል፡፡

ውይይቱ በቀድሞዋ የኒውዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አወያይነት የመንግስት፣ የሲቪክ ማህበራት እንዲሁም የወጣቶች ተወካዮች የተሳተፉበት እንደነበር ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡