የሀገር ውስጥ ዜና

የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዳይከበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Meseret Demissu

October 01, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 21 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዳይከበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 503 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጀኔራል ኮሚሽነር ኮማንደር አራርሳ መርዳሳ እንደገለጹት÷ የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዳይከበር ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት ሰዎች በተጨማሪም የጦር መሳሪያ ተይዟል።