የሀገር ውስጥ ዜና

ባለፉት 24 ሰዓታት 730 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 7 ሰዎች ህይወት አልፏል

By Meseret Demissu

October 01, 2020

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 6 ሺህ 475 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 730 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 76 ሺህ 98 ደርሷል።