ቢዝነስ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ

By Tibebu Kebede

October 02, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ የ400 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር በትዊተር ገጹ እንዳስታወቀው ድጋፉ የከተማ ሴፍቲኔት ፕሮግራምን ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡

ከዚህ ውስጥ 50 ሚሊየን ዶላሩ ስደተኞች በሚገኙበት አካባቢ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ስደተኞች የስራ እድል ፈጠራ የሚውል መሆኑምም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡