Fana: At a Speed of Life!

የቦይንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሃላፊነታቸውን ለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ቦይንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዴኒስ ሙይለንበርግ ሃላፊነታቸውን ለቀቁ።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በኩባንያው ከተፈጠረው ቀውስ ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸው ለቀዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በተለይም ከቦይንግ ማክስ 737 አውሮፕላን ችግር ጋር በተያያዘ በኩባንያው የተፈጠረውን ችግር በአግባቡ መቆጣጠር አልቻሉም ነው የተባለው።

የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድም የእርሳቸው መልቀቅ በኩባንያው ውስጥ ያለውን የስራ መንፈስና በራስ መተማመን ለመመለስ ያግዛል ብሏል።

የ55 አመቱ ሙይለንበርግ ከፈረንጆቹ 2015 ጀምሮ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን አገልግለዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚ ከመሆናቸው ቀደም ብሎ ከፈረንጆቹ 19 85 ጀምሮ በኩባንያው የተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

የኩባንያው ሊቀ መንበርም እርሳቸውን በመተካት ሃላፊነቱን ይረከባሉ ተብሏል።

በቦይንግ በ737 ማክስ አውሮፕላኖች በተፈጠሩ ችግሮች ሳቢያ በሁለት የአውሮፕላን መከስከስ አደጋዎች 346 ሰዎች ህይዎታቸው ማለፉ ይታወሳል።

ከዚያን ጊዜ ወዲህም ኩባንያው አመኔታን አጥቶ ቆይቷል።

በቅርቡም በቀጣዩ ወር ይጀመሩ የነበሩ የማክስ 737 አውሮፕላኖች ምርትን እንደሚያስቆም ገልጾ ነበር።

ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.