ቢዝነስ

ኢትዮጵያ ከመጭው ጥቅምት ወር ጀምሮ በሯን ለቱሪዝም ክፍት ታደርጋለች

By Tibebu Kebede

October 05, 2020

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከመጭው ጥቅምት ወር ጀምሮ በሯን ለቱሪዝም ክፍት እንደምታደርግ ቱሪዝም ኢትዮጵያ አስታወቀ።

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ግርማ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ በቱሪዝሙ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮ ቆይቷል።

ለዚህም በመንግሥት በኩል ለሆቴሎች በአነስተኛ ወለድ ብድር ከማቅረብ ጀምሮ በርካታ ድጋፎች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስረድተዋል።

ሆቴሎችን እና የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎችን ዘግቶ መቀጠል እንደማይቻል የተናገሩት አቶ ስለሺ፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በከፍተኛ ጥንቃቄ በመከላከል ከመጭው ጥቅምት ወር ጀምሮ ቱሪዝምን ክፍት ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።