Fana: At a Speed of Life!

የኪርጊዝታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኩባትቤክ ቦሮኖቭ ስልጣን ለቀቁ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኪርጊዝታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኩባትቤክ ቦሮኖቭ ስልጣን ለቀቁ፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ የሃገሪቱ ፓርላማ አፈ ጉባኤ ዳስታን ጁማቤኮቭም የስልጣን መልቀቂያቸውን አስገብተዋል፡፡

የስልጣን መልቀቂያው የሃገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን ባለፈው እሁድ የተካሄደውን የፓርላማ ምርጫ ውጤት ውድቅ ካደረገ በኋላ የተሰማ ነው፡፡

ኮሚሽኑ የምርጫው ውጤት ተጭበርብሯል በሚል ውድቅ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡

ቀደም ባሉት ቀናት የሃገሬው ዜጎች የምርጫ ውጤቱን በመቃወም አደባባይ ወጥተው ከፀጥታ ሃይሎች ጋር ተጋጭተው ነበር፡፡

ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመተካት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባም ሳዲር ዣፓሮቭን በጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሾሟል፡፡

የተቀናቃኝ ፓርቲ መሪው ዣፓሮቭ በፈረንጆቹ 2013 በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ በፈጸሙት እገታ ምክንያት 11 አመት ከስድስት ወራት የእስር ቅጣት ተበይኖባቸው ማረሚያ ቤት ገብተው ነበር፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.