ሰራተኞች በመጸዳጃ ቤት የሚያሳልፉትን ጊዜ ለማሳጠር የተዘጋጀው የመጸዳጃ ወንበር ንድፍ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣2012 (ኤፍቢሲ) ሰራተኞች ብዙ ጊዜያቸውን መጸዳጃ ቤት እንዳያበክኑ በሚል የተነደፈው መጸዳጃ ወንበር ብዙዎቹን እያወዛገበ ይገኛል፡፡
ረጀም እና ቀላል ስሜትን የሚፈጥር የመፀዳጃ ቤት ቆይታ ሰዎች ጋዜጣዎች እንዲያነቡ እና በስልኮቻቸው ኢንተርኔት እንዲጠቀሙ እድልን ፈጥሮ ቆይቷ፡፡
አሁን በንድፍ ደረጃ ያፋ የሆነው የመፀዳጃ ወንበር ግን ይህን አካሄድ ፍፃሜውን እንዲያገኝ ሊያደርግ ይችላል እየተባለ ነው፡፡
ይህ ንድፍ ይፋ የተደረገው በእንግሊዛዊው አማካሪ መሐንዲስ ማህቢር ጊል ሲሆን አዲሱ ንድፍ በ 13 ዲግሪ ወደታች ያንሸራተታል ይህም በመጸዳጃ ቤት የሚኖረውን ቆይታ ረጅም እንዳይሆን ያደርጋል ነው የተባለው፡፡
በዚህም በአዲሱ የመጸዳጃ ቤት ወንበር ተጠቃሚዎች መቆየት የሚችሉት ከ 5 እስከ 7 ደቂቃ ብቻ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
መሃንዲሱ እንዳሉትም መቀመጫው በተጠቃሚዎች እግሮች ላይ የተወሰነ ስሜት የመረበሽ ስሜትን በመፍጠር ተጠቃሚዎቹ በፍጥነት እንዲነሱ የሚያስገድድ ሲሆን ነገር ግን ጤና ላይ ግን የጎላ እክልን አያስከትል ብሏል፡፡
ጊል ከራሱ መፀዳጃ ቤት ልምድ በመነሳት ይህን ለመስራት እንዳሰበም በመናገር ዲዛይኑ ሰራተኞች በመጸዳጃ ቤት የሚያሳልፉትን ቆይታ በማሳጠር አሰሪዎች ከሰራተኞቻቸው ከፍ ያለ ጊዜን ማግኘት እንዲችሉ ያስችላል ሲል ተናግሯል፡፡
በርካቶችም ለሠራተኞቹ እና ለሰው ልጆች ክብር የጎደለውየ ካፒታሊዝም ፍጹም ውክልና ነው በሚል እየተቹት ይገኛሉ፡፡
መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በብሪታኒያ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎችና የንግድ ተቋማት ሰራተኞች በሚያሳልፉት ረጅም የእረፍት ሰዓት ከሀገሪቱ 4 ቢሊየን ፓውንድ በየዓመቱ ታጣለች፡፡
ምንጭ፡-ኦዲቲሴንተራል
በፌቨን ቢሻው