የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የስራ ጉብኝት ጅማ ገብተዋል

By Tibebu Kebede

October 12, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ጅማ ከተማ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ጅማ አባ ጅፋር አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋርም የኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ እና አማካሪያቸው የማነ ገብረዓብ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነትና የቀጠናው ሀገራት ትስስር ላይ እንደሚወያዩ የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።