የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎበኙ

By Abrham Fekede

October 12, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ፣ የሴቶችና ህፃናት ሚኒስትሯ ፊልሰን አብዱላ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በቅርቡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰበትን አካባቢ ጎበኙ።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 በተለምዶ ቦሌ ሚካኤል አየር አምባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መስከረም 29 ቀን 2013 ዓ.ም በደረሰው የእሳት አደጋ የሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ይታወሳል፡፡