በቡርኪናፋሶ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የ35 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በቡርኪና ፋሶ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የ35 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።
ጥቃቱ በሀገሪቱ አንድ ከተማ ላይ በሚገኝ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ላይ የተፈጸመ መሆኑን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በታጣቂዎች በተፈጸመው በዚህ ጥቃት የ35 ሰዎች ህይወት ማለፉ ነው የተገለጸው።
ከእነዚህ ውስጥም 31 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው በዘገባው ተመላክቷል።
በሰሜናዊ ሶዩም ግዛት አርቢንዳ ከተማ የሀገሪቱ ጦር ጥቃቱን ተከትሎ በወሰደው አጸፋዊ እርምጃ ሰባት ወታደሮችና 80 ታጣቂዎች መገደላቸውም ተነግሯል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሮክ ማርቲን ክርስቲያን የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ የሁለት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን ቀን አውጀዋል ፡፡
ለጥቃቱም እስካሁን ሃላፊነት የወሰደ አካል አለመኖሩ ተመላክቷል።
በፈረንጆቹ 2015 ወዲህ በቦርኪናፋሶ በታጣቂዎች የሚፈጽሙት ጥቃት እየጨመረ መምጣቱን መረጃዎች ያሳያሉ።
በተያዘው ወር መጀመሪያ ላይ በምሥራቅ ቡርኪናፋሶ በቤተክርስቲያን ውስጥ በታጣቂዎች በተከፈተ ጥቃት ቢያንስ14 ሰዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ነው።
ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ