Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር አሚር አማን በሶማሌ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች ጉብኝት አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ከሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በሶማሌ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጉብኝት አደረጉ።

ጉብኝቱ በጎዴ፣ ሸበሌ ዞን እና ቀላፎ ወረዳ የተደረገ ነው።

በጉብኝታቸውም በጎዴ ከተማ ሸበሌ ዞንና ቀላፎ ወረዳ የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ፣ የጤና ተቋማትን እና ተንቀሳቃሽ የጤና ህክምና አቅርቦትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅትም የጤና ሚኒስቴር በጎዴ አጠቃላይ ሆስፒታል የእናቶች እና ህፃናት ህክምና በተሟላ መልኩ በአንድ ማዕከል እንዲሰጥ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ለማደስ ተስማምቷል።

ከዚህ ባለፈም የአይን እና የልብ መመርመሪያ መሳሪያዎች፣ አልትራሳውንድ እና ራጅ በጤና ሚኒስቴር፣ በክልሉ ጤና ቢሮ እና በሆስፒታሉ ተዛማጅ ፈንድ ለመግዛት ስምምነት ላይ መደረሱን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.