የሀገር ውስጥ ዜና

5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን ሰኞ ይካሄዳል

By Abrham Fekede

October 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ሰኞ ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ ስብሰባውን የሚያካሂደው በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው ተብሏል፡፡

በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው፡፡

በልዩ ስብሰባውም የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መስከረም 25፣2013 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽንን ያጸድቃል፡፡